=>ቅድስቷ እናታችን በነገድ እሥራኤላዊ ስትሆን የተወለደችው ኢየሩሳሌም ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ
ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው በሚገባው ፈሊጥ አሳድገው ወደ ትምሕርት አስገቧት::
+አስተማሪዋ ገዳማዊ መነኮስ ነበርና ከተማ ውስጥ አያድርም:: አስተምሯት ዕለቱኑ ወደ በዓቱ ይመለስ ነበር እንጂ:: ዓመተ ክርስቶስ ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቃ ተማረች::
+አንድ ቀን እንደ ልማዷ ልትማር ብትጠብቀውም መምሕሯ ሊመጣ አልቻለም:: ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ መነኮሱን ልትጠይቅ: አንድም ልትማር ወደ በዓቱ ሔደች::
+በሩ ላይ ደርሳ ብታንኩዋኩዋም መልስም: የሚከፍትም አልነበረም:: ከውስጥ ግን ምርር ያለ የለቅሶ ድምጽ ተሰማት:: "ጌታ ሆይ! ይቅር በለኝ?" እያለ በተደጋጋሚ ይጮሃል:: ያ ደጉ መነኮስ ነበር::
+ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ በቅጽበት አንድ ሐሳብ መጣላት:: "እርሱ በንጽሕና እየኖረ ስለ ነፍሱ እንዲሕ ከተማጸነ እኔማ እንደምን አይገባኝ!" ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች:: የለበሰችውን ልብስ አልቀየረችም:: ቤተሰቦቿን አልተሰናበተችም:: ከቤቷ አተር በዘንቢል እና ውሃ በትንሽ እቃ ይዛ ወደ ጐልጐታ ገሰገሰች::
+ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ላይ ወድቃ አለቀሰች:: ጸለየችም:- "ጌታ ሆይ! ነፍሴን ወደ ዕረፍት አድርሳት? ከክፉ ጠላትም ጠብቀኝ? ይሕንን አተርና ውሃ ለእድሜ ዘመን ሁሉ ባርክልኝ::"
+ይሕን ብላ እየፈጠነች ከኢየሩሳሌም ተነስታ በእግሯ ቃዴስን: ሲናይ በርሃን አቁዋርጣ ግብፅ ደረሰች:: ምርጫዋ ብሕትውና ሆኗልና ልምላሜ ከሌለበት: ፀሐዩ እንደ ረመጥ ከሚፋጅበት በርሃ ገባች::
+በዚያም ከያዘችው አተር ለቁመተ ሥጋ እየበላች: ከውሃውም በጥርኝ እየተጐነጨች: ማንንም ሰው ሳታይ በፍጹም ተጋድሎ ለ38 ዓመታት ቆየች:: የቀኑ ሐሩር: የሌሊቱ ቁር (ብርድ) ልብሷን ቆራርጦ ቢጨርሰው እግዚአብሔር ፀጉሯን አሳድጐ አካሏን ሸፈነላት::
+ጊዜ ዕረፍቷ ሲደርስ የቅዱሳንን ዜና የሚጽፈው ታላቁ አባ ዳንኤል ወደ እርሷ ደረሰ:: እንዳያት ተከተላት:: እርሷ ግን በተሰነጠቀ አለት ውስጥ ገብታ ተደበቀች:: አባ ዳንኤል በውጪ ሆኖ ተማጸነ:- "እባክህ አባቴ! ውጣና ባርከኝ" አለ:: ሴት መሆኗን አላወቀም ነበርና:: እርሷ ግን "ራቁቴን ነኝና አልወጣም" አለችው::
+ልብሱን አውጥቶ ሰጥቷት ወጥታ ተጨዋወቱ:: በፈቃደ እግዚአብሔር ዜናዋን ሁሉ አወቀ:: ወደ በዓቷ ዘወር ሲል በዘንቢል የሞላ አተር ተመለከተ:: ለ38 ዓመታት ተበልቶ ዛሬም ሙሉ ነው:: አባ ዳንኤል ይፈትነው ዘንድ ከአተሩ በደንብ በላለት:: ከውሃውም ጠጣለት:: ግን ሊጐድል አልቻለም::
+እያደነቀ "እናቴ ሆይ! ልብሴን ውሰጂው" ቢላት "ሌላ አዲስ አምጣልኝ" አለችው:: ይዞላት በመጣ ቀን ግን ተሠውራለችና አላገኛትም::
+አንድ ቀን ግን (ማለትም ግንቦት 28) አረጋውያን መነኮሳት መጥተው የገጠማቸውን ነገር ነገሩት:: እንዲሕ ሲሉ:- "ሰው ተመልክተን ወደ በዓቱ ስንገባ አተር በዘንቢልና ውሃ በመንቀል አገኘን:: ስንበላው ወዲያው አለቀ::" አባ ዳንኤል ነገሩን ገና ሳይጨርሱለት አለቀሰ::
+አተሩ አለቀ ማለት ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ አርፋለች ማለት ነውና:: አረጋውያኑ ግን ቀጠሉ:- "ከበዓቱ ስንወጣ በጸጉሯ አካሏ ተሸፍኖ ወደ ምሥራቅ ሰግዳ አርፋ አግኝተን ከሥጋዋም ተባርከን ቀበርናት" አሉ:: አባ ዳንኤል ዜናዋን ጽፎላት ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ታከብራታለች::
=>አምላካችን በቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን:: ከበረከቷም ያድለን::
=>ግንቦት 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ ተጋዳሊት (ገዳማዊት)
2.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ሥጋው ቆዽሮስ የደረሰበት)
3.አባ መርቆሬዎስ ገዳማዊ
4.አባ ጌርሎስ (ጻድቅና ሰማዕት)
5."45" ሰማዕታት (የአባ ጌርሎስ ደቀ መዛሙርት)
6.ቅዱስ አጋቦስ ሰማዕት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.አማኑኤል ቸር አምላካችን
2.ቅዱሳን አበው (አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ)
3.ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
4.ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ (ሰማዕት)
=>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>
On this day of the year 43 A.D., the body of St. Epiphanius (His biography is under the 17th. of Bashans), arrived to the island of Cyprus. The boat that carried his body arrived to Cyprus from Constantinople on the 28th. day of Bashans. The priests and the people came with crosses, gospels, candles and incense and carried his body to the church. When they started to dig his tomb, two deacons did not allow them. They were excommunicated by the saints for their bad reputation. The body remained in the church for four days without a change or a stench. His body looked as if he was asleep. A saintly deacon came near the body and said: "I know of your relationship with God, and that you can restrain these evil opponents." He then took an ax and hit the ground with it. The two opposing deacons fell on their faces immediately, and they were carried to their homes and died on the third day.
The body of the Saint was anointed and wrapped, they buried him in a marble sarcophagus in he church. Many miracles appeared from his body.
May his prayers be with us, and glory be to God forever. Amen.

No comments:
Post a Comment