One Lord, One Faith, One Baptism. Eph 4:5

አንድ ጌታ፡ አንድ ሃይማኖት፡ አንዲት ጥምቀት። ኤፌ 4:5

Thursday, 21 May 2015

ስንክሳር ዘግንቦት 14 Ginbot 14 (May 22) IN THE NAME OF THE FATHER AND OF THE SON AND OF THE HOLY SPIRIT, ONE GOD. AMEN.

 በስመ አብ: ወወልድ: ወመንፈስ ቅዱስ: አሐዱ አምላክ
ግንቦት 14
  ቅዱስ ዻኩሚስ (አባ ባኹም)
=>ዛሬን አያድርገውና ምንኩስና ማለት መላእክትን መስሎ የሚኖርበት ሕይወት ነበር:: ምንኩስና በእግዚአብሔር ፈቃድ በአባ እንጦንስ ቢመሠረትም ሕይወቱን በማስፋፋት ደረጃ የቅዱስ ዻኩሚስን ያሕል የደከመና የተሳካለት ግን የለም::
+ቅዱሱ በትውልዱ ግብፃዊ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ከቀደመ ሕይወቱ ጋር በተያያዘ የሚተረክ ነገር በመጽሐፈ ገድሉ ላይ አለ:: ዻኩሚስ ወደ ምንኩስናው ዓለም የመጣ በታላቁ አባ ዸላሞን አማካኝነት ነው:: ለተወሰነ ጊዜም መንፈሳዊ አባቱን እየረዳ ሕይወተ መነኮሳትን አጥንቷል::
+በመንፈሳዊ ሕይወቱና በተጋድሎ እየበረታና እየደረጀ ሲሔድ ከአባ ዸላሞን ተለይቶ: ማሕበር መስርቶ ለመኖር አምላኩን ጠይቆ ፈቃድ በማግኘቱ በሕግ የሚመራ የመጀመሪያውን ገዳም መሥርቷል::
+ቅዱስ ዻኩሚስ ጸሎቱ አጋንንትን ከአካባቢው አያስቀርባቸውም ነበር:: አካሉ አልቆ በአጥንቶቹ እስኪቆም ድረስ ጾሟል:: ዓርብ ዓርብ የጌታችንን ሕማማት እያሰበ ከእንባ ጋር ይሰግዳል:: እንባውና ላበቱ ከፊቱ እየወረደ አካባቢው ጭቃ ይሆን ነበር:: ጌታችንም መስቀል ተሸክሞ ይታየው ነበር::
+ስለ ክብሩም መላእክት ወደ ሰማይ ወስደው ገነትና ሲዖልን አሳይተውታል:: አባታችን ቅዱስ ዻኩሚስ ከርሕራሔው የተነሳ አጋንንት ያደሩባቸውን ሰዎች ሲያገኝ በቀጥታ ከመፈወስ ይልቅ ደዌውን: ርኩሳን መናፍስቱንም ወደ እርሱ እንዲገለበጡ ያዛቸው ነበር::
+ከዚያም በጾም: በጸሎትና በስግደት ያማስናቸዋል:: ያኔ በግዳቸው እየጮሁ ሲወጡ ደጉ አባት "ምነው ትንሽ ቆዩ እንጂ" ይላቸዋል::
+አጋንንቱም እያደነቁ "ከገነት ካስወጣነው ከአዳም በቀር እንዲህ ዓይነት ፍጡርስ ዓይተን አናውቅም" ብለው እንደ ጢስ በነዋል:: አጋንንት ስለሚፈሩት "አርበኛው መነኩሴ" ይሉታል::
+"+ የቅዱስ ዻኩሚስ ፍሬዎች +"+
1.በግብፅ በርካታ ገዳማትን አቁዋቁሟል::
2.ለሁሉም ገዳማት አበ ምኔቶችን ሹሞ እየዞረ ይጠብቃቸው ነበር::
3.የመጀመሪያውን ሥርዓተ መነኮሳት አዘጋጅቷል::
4.መነኮሳት ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ሹመት እንዳይሾሙ ከልክሏል::
5.መነኮሳት ከገዳማቸው በፍፁም እንዳይወጡ ከልክሏል::
6.ከግብፅ ውጪ ምንኩስናን ያስፋፉ አባቶችን አስተምሮ አመንኩሷል:: (ለምሳሌ በኢትዮዽያ ምንኩስናን ያስፋፉት አቡነ አረጋዊ የዚህ አባት ደቀ መዝሙር ናቸው)
+ከዚሕም ባለፈ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል:: ቅዱስ ዻኩሚስ ጫማ ሳይጫማ: እሾህን ሳይሰቀቅ ይረግጥም ነበር:: የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ እጥፍ ሆኖ የበዛለት ቅዱሱ መነኮስ ወደ ወደደው እግዚአብሔር በዚህች ቀን ሔዷል::
=>የጻድቁ መነኮስ ጸጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::
=>ግንቦት 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዻኩሚስ (አበ መነኮሳት ሣልሳዊ)
2.አባ ሲማኮስ ሰማዕት
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት
=>+"+ ይህ ነገር ለተሰጣቸው ነው እንጂ ለሁሉ አይደለም:: በእናት ማሕጸን ጃንደረቦች ሆነው የተወለዱ አሉ:: ሰውም የሰለባቸው ጃንደረቦች አሉ:: ስለ መንግስተ ሰማያትም ራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች አሉ:: ሊቀበለው የሚችል ይቀበለው:: +"+ (ማቴ. 19:11)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>

The Departure of St. Pachomius (Pakhom), the Father of the Spiritual Communal Monastic life (Cenobitic life).

On this day, of the year 64 A.M. (348 A.D.), Abba Pachomius, the father of the spiritual communal life (Cenobitic life), departed. He was born in Thebes (Luxor) from pagan parents, who forced him to worship idols. He rejected and mocked this worship, then became a monk with St. Balamon (Palaemon). He lived in submission to him for many years, and he mastered well the ways of the monastic life. Then the angel of the Lord appeared to him and commanded him to establish a communal and holy monastic life. Many monks gathered together to him, and he built for them many monasteries and established for them a system of manual labor, the times of prayers, and eating. He was the father of them all, with an Abbot in every monastery. He visited all the monasteries, from Aswan to Edfu to Donasa to the end of Upper Egypt to the north. He did not permit any one of his sons to become a priest for the sake of the vainglory of this world, and not to overlook the purpose of their monastic life of worship by being away from the world. He invited a priest from outside for each monastery to officiate the Divine Liturgy. When Pope Athanasius wanted to ordain him a priest, he fled from him. St. Athanasius asked his disciples to tell him that he who built his house on the rock that can not be shaken, and fled from the vainglory of the world, is blessed, and his disciples are also blessed.
He desired once to see Hades, and he saw in a night vision the habitation of the sinners and places of torment.
He remained the father of the Cenobites for forty years. When the time of his departure drew near, he called the monks, strengthened their faith, and appointed someone to take over his place after him, then departed in peace.
May his prayers be with us. Amen.

No comments:

Post a Comment