=>ቅዱስ ወብጹእ እንድራኒቆስ ሐዋርያ ትውልዱ ነገዱ ከቤተ እሥራኤል ሲሆን ከ72ቱ አርድእት አንዱ ነው::
ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ 120 ቤተሰቦቹን ሲመርጥ እርሱን ከአርድእት ጋር ደምሮ አስተምሮታል::
+ሰብዐው አርድእት በጌታችን ተልከው አጋንንት ሲገዙላቸው ከእነርሱ አንዱ ቅዱስ እንድራኒቆስ ነበር:: ይሕ የተፈጸመ ገና መድኃኔ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት ነው:: (ሉቃ. 10:1-20)
+ቅዱሱ ከጌታችን ዕርገት በሁዋላ ከሐዋርያት ጋር ለ10 ቀናት በሱባኤ ሰንብቶ የመንፈስ ቅዱስን ሐብት ተቀብሏል:: እንደ ባልንጀሮቹም ወደ ዓለም ወጥቶ የወንጌል የምሥራችን ሰብኩዋል:: በተለይ ከቅዱስ ዻውሎስ ጋር ለበርካታ ዓመታት አምላኩን አገልግሏል:: ቅዱስ ዻውሎስም በቆረንቶስ እያለ ቅዱስ እንድራኒቆስ በሮም ያስተምር ነበር:: ለዛም ነው በሮሜ መልዕክቱ 16:7 ላይ "እንድራኒቆስን ሰላም በሉ" ያለው::
+ቅዱስ ዻውሎስ በሰማዕትነት ካረፈ በሁዋላ ከቅዱስ ዮልዮስ ጋር ሆነው የአህዛብን ልቡና በወንጌል አብርተዋል:: እጅግ ብዙ መከራ ደርሶባቸዋል:: ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው ትዕግስት ድል ነሥተዋል:: በዚሕም በርካታ የጣኦት ቤቶችን አፍርሰው አብያተ ክርስታያናትን አንጸዋል::
በአሕዛብም ፊት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አሳይተዋል::
+ቅዱስ እንድራኒቆስ ብዙ መከራን ቢቀበልም አንገቱን ይቆረጥ ዘንድ የጌታ ፈቃዱ አልነበረምና ጥቂት ታሞ በዚሕች ቀን አርፏል:: ባልንጀራው (ሐዋርያው) ቅዱስ ዮልዮስ በክብር ገንዞ ቀብሮታል::
+"+ ቅዱስ ያዕቆብ +"+
=>ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ (ታማኝ) የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
+ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ (ጥብዐቱ) ይታወቃል:: በ340ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል:: በዚህም ምክንያት መከራ ተቀብሏል: ታስሯል: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል::
=>የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ ክርስቶስ ጸጋ ክብራቸውን ያድለን::
=>ግንቦት 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ እንድራኒቆስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ (ለክርስቶስ የታመነ)
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ እንጦንዮስ (አበ መነኮሳት)
5.አባ ዻውሊ የዋህ
=>+"+ ስለ እናንተ ብዙ ለደከመች ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ:: በሐዋርያት መካከል ስመ ጥሩዎች ለሆኑ: ደግሞም ክርስቶስን በማመን ለቀደሙኝ: አብረውኝም ለታሰሩ ለዘመዶቼ ለአንድራኒቆንና ለዮልያን (እንድራኒቆስና ዮልዮስ) ሰላምታ አቅርቡልኝ:: +"+ (ሮሜ. 16:6)
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>

On this day, St. Andronicus departed. This disciple was chosen by the Lord to be among the seventy disciples whom He sent before Him to preach the kingdom of God. He received the Holy Spirit in the Upper Room on the day of the Pentecost. St. Paul mentioned his name in (Romans 16:7) saying: "Greet Andronicus and Junia, my kinsmen and my fellow prisoners, who are of note among the apostles, who also were in Christ before me."
He preached the Gospel in many cities in the company of Junia, and they guided many to the Christian faith, and performed many miracles, healed the sick, and transformed the temples of idols to churches. When they completed their course, and the Lord willed to take them from this world, Andronicus became ill for a short time and departed in peace. Junia buried him in a cave, and he prayed to the Lord to take him also. He departed on the next day.
May their prayers be with us and glory be to God forever. Amen.
No comments:
Post a Comment